Fana: At a Speed of Life!

በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ከጉብኝቱ ቀጥሎም ፥ “ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ከየት ወዴት? ” በሚል ርዕሰ-ጉዳይ ተቋሙ ውጣ ውረዶችን በማለፍ እያስመዘገባቸው ያሉ ስኬቶችን የሚዳስስ ጽሑፍ ቀርቦ ምክክር እንደሚደረግበት ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.