የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ይከበራል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ በመጪው ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ አንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።
ምክር ቤቱ 1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም ፥ የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም አንደሚከበር አስታውቋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር በጾም ወቅት ሲያደርግ እንደነበረው እርስ በርስ በመደጋገፍና ለተቸገሩ ወገኖች በማካፈል ሊሆን እንደሚገባም አሳስቧል፡፡
በቤተልሄም መኳንት