Fana: At a Speed of Life!

የአንጀት ቁስለት በሽታ እንዴት ይከሰታል?

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአንጀት ቁስለት በሽታ የምግብ መፍጫ ሥርዓትን አዋኪ መሆኑን የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በሽታው በየትኛውም የዕድሜ ክልል በሚገኙ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን÷ በተለይም በወጣትነትና ጎልማሳነት ዕድሜ ባሉ ሰዎች ላይ በስፋት እንደሚከሰት ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

የአንጀት ቁስለት በሽታ መንስኤ ምንድን ነው?
• በሽታው በምን ምክንያት እንደሚከሰት በትክክል ባይታወቅም÷ የዘር ተጋላጭነት፣ የአኗኗር ሁኔታዎች እና አንጀት ውስጥ የሚገኝ ባክቴሪያ የሚሉት ሳይንሳዊ መላምቶች በመንስኤነት ይተቀሳሉ፡፡

የአንጀት ቁስለት በሽታ አይነቶች
• የአንጀት ቁስለት በሽታ አይነቶች ክሮንስ እና አልሰሬቲቭ ኮላይትስ በመባል ይታወቃሉ፡፡

ክሮንስ የትኛውንም የአንጀት ክፍል (ከአፍ እስከ ፊንጢጣ ሊጎዳ ይችላል)፤ አብዛኛውን ጊዜ የትንሹን አንጀት የመጨረሻ ክፍል (የቀጭን አንጀትን ጫፍ) እና ትልቁ ን አንጀት ያጠቃል፡፡

የክሮንስ በሽታ ምልክቶችም የሆድ ህመም፣ ክብደት መቀነስ፣ ድካም እና የሰገራ መልክ መቀየር ናቸው፡፡

ክሮንስ ሙሉ የአንጀት ንብርብሮችን የማጥቃት አዝማሚያ ስላለው ፌስቱላ እንዲፈጠር እንደሚያደርግም ይነገራል፡፡

• አልሰሬቲቭ ኮላይተስ የሚባለው የአንጀት ቁስለት በሽታ ደግሞ ትልቁን አንጀት ወይም ፊንጢጣን ብቻ እንደሚያጠቃ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡

ከበሽታው ምልክቶች መካከልም÷ ተቅማጥ፣ ደም እና ንፍጥ የቀላቀለበት ሰገራ እና የሆድ ቁርጠት ይገኙበታል፡፡

የበሽታውን መከሰት እንዴት ማወቅ ይቻላል?
• የደምና የሰገራ ምርመራ፣ ኢንዶስኮፒ ፣ የሆድ ራጅ እና ሲቲ ስካን እንዲሁም የሆድ አልትራሳውንድ ምርመራዎች በማድረግ የበሽታውን መከሰት ወይም አለመከሰት ማወቅ እንደሚቻልም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአንጀት ቁስለት በሽታ ሕክምና
• እንደ ህመሙ ደረጃ የሚሰጡ የተለያዩ ሕክምናዎች መኖራቸውንም ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.