Fana: At a Speed of Life!

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር ዛሬ በስልክ ተወያይተዋል።

በነበራቸው የስልክ ውይይት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ታሪካዊ ወዳጅነት ይበልጥ በማጠናከር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በትብብር ለመከላከል በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

በውይይቱ ወቅት አቶ ገዱ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ያደረጓቸውን ውይይቶች እንዲሁም በአሁኑ ስዓት የግድቡ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሶስቱ ሀገራት ከግድቡ ጋር በተያያዘ ያላቸውን ልዩነት በውይይት መፍታት አለባቸው ብለው እንደሚያምኑም የደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ናሌዲ ፓንዶር በነበራቸው የስልክ ውይይት ገልጸዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.