Fana: At a Speed of Life!

ሩሰያ በምዕራቡ ዓለም ለሚጣለው ማዕቀብ መፍትሄዎች እንዳሏት ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሰያ በምዕራቡ ዓለም ለሚጣለው ማዕቀብ ብሪክስን ጨምሮ ባለብዙ ወገን መፍትሄዎችን እንደምትጠቀም አስታውቃለች፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በቻይና የሁለት ቀናት ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

በጉብኝታቸው ወቅት ከቻይናው አቻቸው ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን፥ ሁለቱ ወገኖች ከመከሩባቸው ጉዳዮች መካከልም የምዕራቡ ዓለም በሁለቱ ሀገራት ላይ በጣሉባቸው ማዕቀብ መፍትሄ በማበጀት ላይ ነውም ተብሏል፡፡

ሰርጌ ላቭሮቭ በቅርቡ ኢትዮጵያ የተቀላቀለችው ብሪክስ እና የሻንጋይ ትብብር ድርጅት (ኤስ ሲ ኦ) ያሉ ባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመጠቀም ከምዕራባውያን ማዕቀብ የሚነሱ ችግሮችን ማሸነፍ መቻሉን ገልጸዋል።

ቀደም ሲል ሩሲያን፣ ብራዚልን፣ ሕንድን፣ ቻይናን እና ደቡብ አፍሪካን ያቀፈ የነበረውና በአሁኑ ወቅት የአባላቱ ቁጥር እየጨመረ የሚገኘው የብሪክስ ትብብር የምዕራባውያን ማዕቀብ ሩሲያ ላይ የሚያሳርፈውን ጫና በመቀነስ በኩል እገዛ እያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል።

በፈረንጆቹ 2022 በሩሲያና ዩክሬን መካከል ግጭት መጀመሩን ተከትሎ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ ህብረት እና በሌሎች ምዕራባውያን ሀገራት በሩሲያ ላይ ከባድ ማዕቀቦች ከተጣሉ ወዲህ የብሪክስ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩም ነው የተነሳው፡፡

ይህም የብሪክስ አባል ሀገራት ከሩሲያ ጋር ያላቸውን የንግድ ልውውጥን ከፍ ማድረጉም ተሰምቷል፡፡

ላቭሮቭ ከቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ጋር ከተወያዩ በኋላ በሰጡት መግለጫ፥ አቻቸውን የማዕቀቡን ውጤት ለመሰረዝ የሚያስችል ቀመር ፈጥረዋል ሲሉ አሞካሽተዋል።

በአንድ ወገን ማዕቀብ ህገ-ወጥ ፖሊሲ ምክንያት የተፈጠሩት የኢኮኖሚ ክፍተቶች በብሪክስ እና በኤ ሲ ኦ ማዕቀፍ እንደሚፈቱ ላቭሮቭ ተናግረዋል።

ለምዕራቡ ዓለም ማዕቀብ ምላሽ ለመስጠት ሩሲያ የውጭ ንግዷን ወደ እስያ-ፓሲፊክ ገበያ እያማተረች ሲሆን፥ ቻይናም ቁልፍ ተዋናይ መሆኗ ተነስቷል፡፡

ባለፈው ዓመት የሩስያ-ቻይና የንግድ ልውውጥ ወደ 240 ቢሊየን ዶላር ከፍ ያለ ሲሆን፥ ይህም ሁለቱ መንግስታት ካቀዱት 200 ቢሊየን ዶላር በላይ ብልጫ አለው ብሏል የቻይና የጉምሩክ መረጃ።

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ጸሃፊ የሆኑት ጃኔት የለን በቻና ባደረጉት የቀናት ጉብኝት የቻይና ኩባንያዎች ለሩሲያ ጦር መሳሪያዎችን ካቀረበ ከፍተኛ መዘዝ ይደርስባቹሃል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

በታኅሳስ ወር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በሚቀጥሉ የውጭ ተቋማት ላይ ማዕቀብ የሚጣልበትን የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.