Fana: At a Speed of Life!

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲያከብር የጋራ ግብረ ኃይሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ ከወዲሁ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን አስታውቋል፡፡

ግብረ-ኃይሉ የኢድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል፡፡

የጋራ ግብረ ኃይሉ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያከብር በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከወዲሁ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር በመግባት ተልዕኮውን በተገቢው እየተወጣ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

ሰላም ወዳዱ የኢትዮጵያ ሕዝብም ለሰላምና ደኅንነት እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን ለማስወገድ በሚካሄደው የፀጥታ ማስከበር ሥራ ውስጥ በባለቤትነት እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል፡፡

የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት የሚያደፈርሱ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ከግብረ-ኃይሉ ጎን ሆኖ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣም ግብረ-ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የሀገርንና የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ በማበርከት የኢትዮጵያን ልዕልና ለማረጋገጥ ሌት ተቀን እየሠሩ ላሉ በግዳጅ ላይ ለሚገኙ የፀጥታ አካላት አመራሮች እና አባላትም ግብረ-ኃይሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.