Fana: At a Speed of Life!

የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት በልብ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ፕዬሬ ንኩሩንዚዛ በ55 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገለፀ።

ፕሬዚዳንት ፕዬሬ ንኩሩንዚዛ በድንገተኛ የልብ ህመም ሀይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

ፕሬዚዳንቱ በትናንትናው እለት በልብ ህመም ተጠቅተው ሆስፒታል ገብተው ህክምና ሲከታተሉ እንደነበረም የሀገሪቱ መንግስት በትዊተር ገፅ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

በአውሮፓውያኑ በ1963 የተወለዱት ፕሬዚዳንት ፕዬሬ ንኩሩንዚዛ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2005 ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ቡሪንዲን መርተዋል።

ፕሬዚዳንት ፕዬሬ ንኩሩንዚዛ የፊታችን ነሃሴ ወር ላይ የፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸውን በባሳለፍነው ግንቦት ወር በተካሄደው ምርጫ ላሸነፉት ኤቫርስቲ ንዳይሽሜ እንደሚያስረክቡ ይጠበቅ ነበር።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.