Fana: At a Speed of Life!

110 የሽብር ቡድኑ ሸኔ አባላት በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በተለየዩ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 110 የአሸባሪው ሸኔ አባላት መንግስት ያቀረበውን የሳላም ጥሪ ተቀብለው እጃቸውን ሰጥተዋል።

የዞኑ አስተዳደር እንዳስታወቀው÷የመንግስት ጸጥታ ሃይሎች በተለያዩ ወረዳዎች በሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኑ ሸኔ አባላት ላይ የተቀናጀ እርምጃ እየወሰዱ ነው፡፡

በተወሰደው የተጠናከረ እርምጃም 2 ሺህ 237 የሸኔ አባላት ሲደመሰሱ ÷89 የሚሆኑት ደግሞ መማረካቸው ነው የተገለጸው፡፡

በተመሳሳይ 110 የሸኔ አባላት መንግስት ያቀረበውን ጥሪ ተቀብለው በሰላም እጃቸውን መስጠታቸው ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል የሽብር ቡድኑ አባላት ማህበረሰቡን ለማሰቃየት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸው ተጠቁሟል፡፡

በዚህ መሰረትም 1 ሞርታር፣ 3 ዲሽቃ፣ 197 ክላሽንኮቭ፣ 8 መድፍ፣ 103 ቦምብ፣ 2 የጦር ሜዳ መነጽር፣ 324 የብሬን ጥይት፣ 482 የዲሽቃ ጥይት እና 10 ሺህ 254 የተለያዩ ጥይቶች መያዛቸው ተጠቅሷል፡፡

በሸኔ ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ የሕዝቡ ሰላም እየተመለሰ መሆኑን የገለጸው አስተዳደሩ÷ በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.