Fana: At a Speed of Life!

በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 345 ሽጉጥ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻውን ምዕራብ ጎንደር ሸህዲ ሽንፋ አድርጎ ወደ ባህርዳር ከተማ ሊገባ የነበረ 345 ሽጉጥ መያዙን የባህርዳር-ጎንደር ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።

ሕገ-ወጥ ሽጉጡ በተሽከርካሪ ላይ ተመሳስሎ በተሰራ ሻግ በድብቅ ተጭኖ ሲጓዝ በተደረገ ክትትል ምሽት 1 ሰዓት ላይ ባህርዳር ከተማ ሊገባ ሲል መያዙ ተገልጿል፡፡፡

ከድርጊቱ ጋር በተያያዘም የመኪናው ሹፌርና ረዳቱ በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

ሽጉጡ ሕገ-ወጥ የመሳሪያ ዝውውሩን በበላይነት በሚመራውና ለጊዜው በቁጥጥር ስር ባልዋለው በተሽከርካሪው ባለንብረት አማካኝነት ወደ ባህርዳር ገብቶ ለጥፋት ዓላማ ሊውል እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.