Fana: At a Speed of Life!

እንግሊዝ በሀገሪቱ የሚገኙ ስደተኞችን በሩዋንዳ ማስፈር ልትጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እንግሊዝ በሀገሪቱ የሚገኙ ስደተኞችን በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ሩዋንዳ በመመለስ ማስፈር እንደምትጀምር አስታወቀች፡፡

ውሳኔው የእንግሊዝ ፓርላማ ሩዋንዳ ለስደተኞች ምቹ ሀገር መሆን አለመሆኗን ውሳኔ ባልሰጠበት አግባብ በጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ይሁንታ የተወሰነ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው÷በሺዎች የሚቆጠሩ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሩዋንዳ መስፈር ይጀምራሉ፡፡

ውሳኔው በእንግሊዙ ጠቅላይ ሚስቴር ሪሺ ሱናክ እና በሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የተደረሰ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

እቅዱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ ከእንግሊዝ ፓርላማ አባላት እና ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተቃውሞ እንደገጠመው አርቲ ዘግቧል፡፡

እንግሊዝ በፈረንጆቹ 2022 ስደተኞችን በሩዋንዳ ለማስፈር ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ብትስማማም ከአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍ/ ቤት ተቃውሞ መቅረቡን ተከትሎ ስምምነቱ ተግባራዊ ሳይደረግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.