Fana: At a Speed of Life!

የኮሪደር ልማት በሚሠራበት አካባቢ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሪደር ልማት ሥራ በሚሠራበት አካባቢ የተቀናጀ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ገበየሁ ሊካሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ከኮሪደር ልማቱ ጎን ለጎን የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳይቋረጥ ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም አስረድተዋል፡፡

ከዚህ በፊት የተቀናጀና ቋሚ ቦታ ባለመኖሩ የተሠራው ሥራ ተመልሶ ሲፈርስ እንደነበር አስታውሰው÷ አሁን ላይ በተጠና መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀጣይም የእግረኛ መንገድን መቆፈር ሳያስፈልግ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማትን ከመሬት ሥር ለመዘርጋት እንደሚያስችል ነው ያመላከቱት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.