Fana: At a Speed of Life!

በሁሉም ዘርፎች ሰራዊቱን የመገንባት ሂደት ተጠናክሮ ይቀጥላል – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም ዘርፎች ኢትዮጵያን የሚመጥን ሰራዊት የመገንባት ሂደት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለቤላ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ ባስቀመጡበት ጊዜ እንደገለጹት÷ የመከላከያ ሰራዊቱን በአደረጃጀት፣ እውቀትና ቴክኖሎጂ የመገንባቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ሰራዊቱ በሁሉም ዘርፎች ብቁ ሆኖ እንዲገኝ እንደሚሰራም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገልጸዋል፡፡

የሠራዊቱን ዕድገት የሚመጥን የመሠረተ ልማት ግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው፤ በዛሬው ዕለት የግንባታው ሂደት የተጀመረው ሆስፒታልም የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል።

ብቃትና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ መሠረት መሆኑን ገልጸው÷ የመሠረተ ልማት መስፋፋት የሠራዊቱን ግንባታ ከማሳለጥ አንጻር ሚናው የጎላ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.