Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅና የስዊዘርላንድ ፕሬዚዳንት ዓለም አቀፍ የትብብር መድረክን ከፈቱ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እና የስዊዘርላንድ ፕሬዚዳንት ቪዮላ አምኸርድ ሦስተኛውን ዓለም አቀፍ የትብብር መድረክ በባዝል ከተማ ከፍተዋል።

ፕሬዚዳንቶቹ ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይትም በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ሰፊ ግንኙነት እንዲሁም በአውሮፓ እና አፍሪካ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በስዊዘርላንድ የልማትና ትብብር ኤጀንሲ የተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የትብብር መድረክ ዘንድሮ ‘ሰላም ምንድን ነው?’ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ሲሆን፤ ለሰላም ግንባታ ቁርጠኛ መሆኑ ተመላክቷል።

ፕሬዚዳንት አምኸርድ የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ላይ ያላቸው ተፅእኖ እያደገ መምጣቱን ገልጸው፤ ይህም ለኢኮኖሚ ልውውጥ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

ስዊዘርላንድ ለአፍሪካ ልማት ቁርጠኝነት እንዳላት ያነሱት ፕሬዚዳንቷ፤ የአፍሪካ ቀንድ የትብብር ፕሮግራም አካል የሆነው የስዊዘርላንድ ልማት ትብብር (ኤስዲሲ) በኢትዮጵያ እንደሚገኝ አንስተዋል።

የልማት ትብብሩ ቆላማ በሆኑ የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የኑሮ ማሻሻያ ስራዎች ስራዎች ላይ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ትብብር ማድረግ ከስዊዘርላንድ አንፃር ጠቃሚ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቷ፤ በተለይም ስዊዘርላንድ በአፍሪካ ህብረት የሚደገፈውን የአፍሪካ ሰላምና ደህንነት መርሆዎችን እንደምትደግፍ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.