Fana: At a Speed of Life!

በአምላክ ቢያድግልኝ የ4ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ድምጻዊ በአምላክ ቢያድግልኝ የ4ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር አሸናፊ ሆኗል፡፡

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 4ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፋና ላምሮት የድምጻውያን ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

በፍጻሜ ውድድሩም በአምላክ ቢያድግልኝ፣ ትዕግስት አስማረ፣ ሄኖክ ብርሃኑ እና ሃብታሙ ይሄነው የተዘጋጁበትን ሥራ በማቅረብ ብርቱ ፉክክር አድርገዋል፡፡

በዚህም በአምላክ ቢያድግልኝ ውድድሩን በአንደኝነት በማጠናቀቅ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡

እንዲሁም ፣ ሃብታሙ ይሄነው 2ኛ፣ ሄኖክ ብርሃኑ 3ኛ እና ትዕግስት አስማረ ደግሞ 4ኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡

በዚህ መሰረትም 2ኛ ለወጣው ሃብታሙ ይሄነው 1ሚሊየን ብር ፣ 3ኛ ሆኖ ላጠናቀቀው ሄኖክ ብርሃኑ 500 ሺህ ብር፣ 4ኛ ለወጣችው ትዕግስት አስማረ 300 ሺህ ብር ተሸልመዋል፡፡

በአጠቃላይ ለ4ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍጻሜ ውድድር የ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡

በሌላ በኩል ለግጥም እና ዜማ ደራሲ ለሆኑት ጸጋዬ ደቦጭ ደግሞ በዘርፉ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የ200 ሺህ ብር ስጦታ አበርክቷል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.