Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ መድን መቻልን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን መቻልን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች አብዱልከሪም መሃመድ ሲያስቆጥር÷ሽመልስ በቀለ ደግሞ የመቻልን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ወልቂጤ ከተማ እና ሻሸመኔ ከተማ ቀን 10 ሰዓት ላይ ያደረጉት ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቅቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.