Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሻድሊ ሃሰን በክልሉ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሃሰን በኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የጋራ የሰላምና የልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸውም÷ በዑራ ወረዳ ባሮ ቀበሌ እየተገነባ ያለውን ትምህርት ቤት እና በአሶሳ ከተማ በግንባታ ላይ የሚገኘውን ባለ አራት ወለል የማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሕንጻ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል፡፡

በማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ አማካኝነት በክልሉ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች የሁለቱን ክልሎች ሕዝቦች አንድነት የበለጠ እንደሚያጠናክሩም አቶ አሻድሊ ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱም በጥራት ተገንብቶ ለሕዝቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችል በቅንጅት እየተሠራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ሥራ ከጀመረ አንስቶ የሁለቱን ክልሎች ሕዝቦች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመንገድ መሰረተ-ልማቶችን እያከናወነ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል የጋራ የሰላም እና የልማት ማስተባሪያ ጽሕፈት ቤት አሶሳ ቅርንጫፍ ኃላፊ ዲንሳ በየነ ናቸው፡፡

ለአብነትም ምሥራቅ ወለጋን ከካማሽ ዞን ወረዳዎች የሚያገናኙ መንገዶችን ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.