Fana: At a Speed of Life!

በሮተርዳም ማራቶን አትሌት አሼቴ በከሪ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኔዘርላንድስ ሮተርዳም ማራቶን አትሌት አሼቴ በከሪ አሸንፋለች፡፡

አትሌቷ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ30 ሴኮንድ  በመግባት ነው ውድድሩን ቀዳሚ ሆና ያጠናቀቀችው፡፡

ኬንያውያኖቹ ቮይላ ኪቢዮት እና ሴሊ ኪፔይጎ ሁለተኛ እና ሶሰተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡

በወንዶች ደግሞ አምደወርቅ ዋለልኝ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ45 ሴኮንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ ሌላኛው አትሌት ብርሃኑ ለገሰ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ16 ሴኮንድ በመግባት ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡

ትውልደ ሶማሊያዊው እና ለኔዘርላንድስ የሚሮጠው አብዲ ናጊየ ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.