Fana: At a Speed of Life!

በኢራንና በእስራኤል መካከል የተፈጠረው ውጥረት የነዳጅ ዋጋ ላይ ተጽዕኖ አለማሳረፉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢራንና በእስራኤል መካከል የተፈጠረው ውጥረት በዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ተጽዕኖ ባለማሳረፉ በእስያ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ መቀነሱ ተገለፀ፡፡

ዓለም ዓቀፉ የነዳጅ ዋጋ ተመን አውጭ የሆነው ብረንት ኦይል እንዳስታወቀው÷ የነዳጅ ዋጋ ከወትሮው የዋጋ መቀዛቀዝ ያሳየ ሲሆን አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት እስከ 90 ዶላር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

ባለፉት ስድስት የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ የነበረ ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ ኢራን በእስራኤል ላይ የሚሳኤል ጥቃት ከወሰደች በኋላ የነዳጅ ዋጋ መቀዛቀዝ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

የኢነርጂ ተንታኙ ቫንዳና ሃሪ÷ በእስያ ያለው የነዳጅ ግብይት ስርዓት በመካከለኛው ምስራቅ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን የአቅርቦት ችግር ከግምት ውስጥ አለማስገባቱን ተናግረዋል።

በእስራኤል እና ፍልስጤም እንዲሁም በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ነጋዴዎች ወደ ገበያው በብዛት አለመሳተፋቸውን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ከ90 ዶላር በታች ዝቅ ሊል እንደሚችልም ተጠቁሟል፡፡

በተለይም እስራኤል ለተፈፀመባት ጥቃት መልስ የምትሰጥ ከሆነ በዓለም የነዳጅ ገበያ ላይ ተጨማሪ መስተጓጎል ሊፈጠር እንደሚችል መነገሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.