Fana: At a Speed of Life!

ዩኤስኤአይዲ ለኢትዮጵያ የ60 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅ (ዩኤስኤአይዲ) ለኢትዮጵያ የ60 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጓል፡፡
 
ድጋፉ “ፊድ ዘ ፊውቸር ኢትዮጵያ ሃይላንድስ” ለተሰኘ የመቋቋሚያ ፕሮግራም እንደሚውል ተመላክቷል።
 
ፕሮግራሙ 120 ሺህ ለሚሆኑ በሴፍቲኔት ፕሮግራም የተመረቁ ተጋላጭ አባወራዎችን ከገበያ እና ገንዘብ ጋር በማገናኘት ሕይወታቸውን ለማሻሻል ያስችላል ተብሏል።
 
ፕሮግራሙ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በሜርሲ ኮርፕስ እና በ5 ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅቶች እንዲሁም ሁለት የቴክኒክ አጋሮች ድጋፍ እንደሚመራ ተጠቁሟል።
 
ፕሮጀክቱ በአማራ፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተጠቅሷል፡፡
 
የዩኤስኤአይዲ የኢኮኖሚ እድገትና የመቋቋም ጽ/ቤት ዳይሬክተር አምበር ሊሊ ኬኒ÷ፕሮግራሙ በርካታ ኢትዮጵያውያንን እንደሚያግዝ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
 
ፕሮግራሞቹ ለከፋ ድህነት ተጋላጭ የሆኑ የገጠር ቤተሰቦችን የመቋቋም አቅምን እንደሚያሳድጉ መግለጻቸውንም በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.