Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም “ቴሌ ብር ኢንጌጅ” የተሰኘ አገልግሎት አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ተጨማሪ ተግባራትን በቴሌብር ሱፐርአፕ መከወን የሚያስችል “ቴሌ ብር ኢንጌጅ” የተሰኘ አገልግሎት አስጀምሯል።

አገልግሎቱ ያለ ኢንተርኔት ክፍያ በደንበኞች መካከል መረጃዎችን መለዋወጥ ፣ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ክፍያዎችን መፈጸም እና መሰል አገልግሎቶችን ማግኘት ያስችላል ተብሏል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ÷ ቴሌ ብር ኢንጌጅ ሕይወትን የሚያቀል እና ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያደርገውን ግስጋሴ የሚያቀላጥፍ ነው ብለዋል።

“ቴሌ ብር ኢንጌጅ” እንደ ማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃዎችን መለዋወጥ የሚያስችል ሲሆን ÷ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እና ድምጾችን መላላክ እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.