Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 192 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ በሳውዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ሥራ 1 ሺህ 192 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ከተመላሾች  ውስጥ 1 ሺህ 78 ወንዶች፣ 89 ሴቶች እና 5 ዕድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ታዳጊዎች  እና 20 ጨቅላ ህፃናት እንደሚገኙ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ቀናት በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከ3 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.