Fana: At a Speed of Life!

ሳፋሪኮም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ጋር  በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዲጂታል ዘርፍ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር ) የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዊሊያም ቫንሄሌፑቴ ጋር በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህ ወቅት በለጠ ሞላ (ዶ/ር )÷ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን በመስራት ውጤት ያስመዘገበ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከተቋሙ ጋር አጋርነት በመፍጠር በተለያዩ  ዘርፎች ላይ በትብብር በመስራት በሀገራዊ ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ፈጣን ለውጥ ለማምጣት እንሰራለን ነው ያሉት፡፡

በተለይ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑ ዘርፍ ትልቅ ሚና ያለው ሳፋሪኮም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እቅድ የተሳካ እንዲሆን በሚደረገው ጥረት በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ዊሊያም ቫንሄሌፑቴ  በበኩላቸው÷ኢትዮጵያ ሰፊ ኢንቨስትመንት አቅም ያላት ሀገር መሆኗን ጠቁመው ከሚኒስቴሩ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ሰፊ ሥራዎችን እየሰሩ መሆኑ ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው ÷ በቀጣይ በተለያዩ የትብብር መስኮች በጋራ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን  የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.