Fana: At a Speed of Life!

በህንድ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው ተባለ።

በሃገሪቱ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ አዲስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መገኘታቸውንም ባላስልጣናቱ አስታውቀዋል።

የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ባለፉት 24 ሰአታት 9 ሺህ 985 አዳዲስ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልጿል።

ከዚህ ባለፈም 274 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው ያለው።

እስካሁን በሃገሪቱ 276 ሺህ 583 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፥ 7 ሺህ 745 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

የሃገሪቱ መንግስት ምግብ ቤቶችን ጨምሮ፣ ትላልቅ መገበያያ ስፍራዎችን እና ቤተ አምልኮዎችን ለመክፈት እንቅስቃሴ ላይ ነበር ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ ግን የባቡር ትራንስፖርት፣ የሃገር ውስጥ በረራ፣ ሱቆችና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች በከፊል አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገልጿል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.