Fana: At a Speed of Life!

በኮሪደር ልማት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምክንያት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጋቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት፡-

• ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

• ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

• ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

• ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች ምክንያት ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ መከልከሉንም ነው ፖሊስ ያሳሰበው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.