Fana: At a Speed of Life!

የሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ፡፡

ዛሬ ምሽት ከሚደረጉት መርሐ ግብሮች ባርሴሎና በሜዳው ኑ ካምፕ የፈረንሳዩን ፓሪስ ሴንት ዠርሜይንን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃሉ፡፡

ባለፈው ሳምንት ሁለቱ ቡድኖች በፓሪስ ፓርክ ዴስ ፕሪንስ ባደረጉት ጨዋታ ባርሴሎና 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል የስፔኑ አትሌቲኮ ማድሪድ ከጀርመኑ ቦሪሲያ ዶርትመንድ ጋር ያሚያደረጉት የመልስ ጨዋታም ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል፡፡

በመጀመሪያው ዙር አትሌቲኮ ማድሪድ በሜዳው ሜትሮፖሊታኖ ዶርተመንድን 2 ለ 1 ያሸነፈ ሲሆን÷ ዛሬ በሲግናል ኢዱና ፓርክ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል ተብሎ ይገመታል፡፡

ሁለቱም ጨዋታዎች ምሽት 4፡00 የሚደረጉ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.