Fana: At a Speed of Life!

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት ያደረገ ‘አስተውሎት’ የተሰኘ ፊልም ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ‘አስተውሎት’ የተሰኘ ፊልም በዛሬው እለት ተመርቋል።

በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ሰውኛ ፕሮዳክሽንና ኢንተርቴይመንት አማካኝነት የተዘጋጀው ‘አስተውሎት’ ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የተሰሩ ሮቦቶችንና ሰዎች በጥምረት የሰሩት ፊልም ነው ተብሏል፡፡

ፊልሙ በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።

በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር) ፊልሙ የተሻለ ነገን እንድናይ ዛሬን ከትናንት በተሻለ እንድንኖር የሚያግዝ ነው ብለዋል።

በቅድስት አባተ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.