Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የኃይል ትስስር በመፍጠር የመሪነት ሚና እየተጫወተች መሆኑ ተጠቆመ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የኃይል ትስስር በመፍጠር የመሪነት ሚና እየተጫወተች መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር ኢ/ር) አስታወቁ ፡፡

በአቡዳቢ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከሚያዝያ 16 እስከ 18 ቀን 2024 እየተካሄደ በሚገኘው ወርልድ ፊውቸር ኢነርጂ ስብሰባ የጎንዮሽ መድረክ ላይ በመገኘት ገለጻ ያደረጉት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የኃይል ትስስር በመፍጠር የመሪነት ሚና እየተጫወተች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቀጠናዊ የሀይል ትስስር መሰረት የመጣልና የማጠናከር ጉዳዮች ኢትዮጵያ በቀጠናው ለትብብርና ቅንጅት የሰጠችውን ትኩረት የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸው እንደተጨማሪ ማሳያም ሱዳናውያን የገጠማቸው ውስጣዊ ችግር ክፍያ እንዲፈጽሙ ባያስችላቸውም የሀይል አቅርቦት መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን የምስራቅ አፍሪካ ፓወር ፑል ለማጠናከርና ለማስቀጠል አይነተኛ ሚና እየተጫወተች ነው ያሉ ሲሆን÷ የኃይል መስመሮች መንገዶችና የቴሌኮም ኔትወርኮችን የመሳሰሉ መሰረተልማቶች ወደ ጎረቤት ሀገራት ተዘርግተው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ብሔራዊ እቅድ ቀጠናዊ ቅንጅታዊ እስትራቱጂ መካተቱንና በአህጉር ደረጃ ማሳደግ ታሳቢ መደረጉን አንስተው፤ እንደሀገር ያለን የሀይድሮፓወር እምቅ አቅምና የማልማት ልምድ፤ እንዲሁም በሃድሮ ፓወር ልማት የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ተቋም መገንባት መቻሉ፤ የምስራቅ አፍሪካ የአረንጓዴ ኢነርጂ ማእከል ለመሆን እንድንሰራ አስችሎናል ነው ያሉት፡፡

የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት በመተግበር የግሉን ዘረፍ በሃይል ልማት ዘርፍ ለማሳተፍ ያለውን ቁርጠኝነት አንዱ ማሳያ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አህጉራዊ የኃይል ሲስተም ማስተርፕላን መሰረት በማድረግ ለሶስት ጎረቤት ሀገራት የሀይል ትስስር መፈጠሩንና ሌሎችን ሀገራትን በማካተት ወደ አህጉራዊ ትስስር ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የኃይል መሠረተልማት ግንባታና ዝርጋታ ከፍተኛ መዋእለንዋይ የሚጠይቅ በመሆኑ የልማት አጋሮች ቁርጠኝነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስታውሰው ኢትዮጵያ ውስጥ በሀይል ልማት ኢንቨስትመንት መሰማራት በቀጠናው የስራ እድል ፈጣራ እና የሰላምና የጸጥታ ጉዳች ላይ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው ብለዋል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.