Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆዜ ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ጉዳዮች እና በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በተመለከተ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም አዲስ አበባ ከተማ ከአሜሪካ ከተሞች ጋር ያላትን የእህትማማችነት ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውን ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.