Fana: At a Speed of Life!

ዊንጉ አፍሪካ በኢትዮጵያ የገነባው ዳታ ማዕከል ዓለም አቀፍ መመዘኛ በማሟላቱ የምስክር ወረቀት አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዊንጉ አፍሪካ በ50 ሚሊየን ዶላር ወጪ በኢትዮጵያ የገነባው ዳታ ማዕከል ዓለም አቀፍ የመመዘኛ መስፈርቶችን በማሟላት የምስክር ወረቀት አገኘ።

ዓለም አቀፍ ምዘና ሲደረግለት ቆይቶ የ”ቲር” 3 ደረጃን በማሟላት የምስክር ወረቀት ያገኘው ማዕከሉ÷ ለመንግሥትና የግል ተቋማት ደኅንነቱ የተጠበቀ ፈጣን እና አስተማማኝ የመረጃ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴዔታ ይሽሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር)÷ ማዕከሉ የምስክር ወረቀት ማግኘቱ በዓለም ገበያ ያለውን ተወዳዳሪነት ከማጎልበት ባለፈ የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር የሚያፋጥን መሆኑን አንስተዋል፡፡

የዊንጉ አፍሪካ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንቶኒ ቮስካርዲስ የምስክር ወረቀት መገኘቱ በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ይከፍታል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ አቅሟን ለማሳደግና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመወዳደር እንደሚያስችላት ጠቅሰዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.