Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በበልግ ወቅት የጎርፍ አደጋ ይከሰትባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በበልግ ወቅት ናዳና የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ይችላል ተብለው በተለዩ 148 ቀበሌዎች የክልሉ መንግስት የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እየሰራ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ገለጸ፡፡

የክልሉን የ100 ቀን ዕቅድ ሂደት በተመለከተ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ሰናይት ሰለሞን በሰጡት መግለጫ÷ክልሉ በበልግ ወቅት ሊከሰት የሚችል የጎርፍ አደጋን ለመከላከል ስጋት የሆኑ 148 ቀበሌዎችን ለይቶ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

አካባቢዎቹም በጌዴኦ፣ በወላይታ፣ በአሌ፣ በቡርጂ፣ በጋሞ፣ በጎፋ፣ በኮንሶ፣ በአሪና ባስኬቶ ውስጥ የሚገኙ ናቸው ብለዋል።

በተጨማሪም በ2017 የትምህርት ዘመን ለሁሉም ተማሪ መፅሐፍትን ለማዳረስ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ በክልሉ የሚገኙ የመንግስት አመራሮችም የወር ደሞዛቸውን ለዚህ ዓላማ ስኬት መልቀቃቸውን አንስተዋል፡፡

ከእነዚህ ተግባራት ባሻገር ክልሉን የኢንቨስትመንት ማዕከል ለማድረግ በቀጣይ የኢንቨስትመንት ፎረም እንደሚያዘጋጅም ሃላፊዋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል።

በጥላሁን ሁሴን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.