Fana: At a Speed of Life!

ለመዲናዋ ነዋሪዎች 143 ሚሊየን ሜትር ኪዩቢክ ውኃ ቀርቧል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከገፀ-ምድርና ከርሰ-ምድር የውኃ መገኛዎች 143 ነጥብ 81 ሚሊየን ሜትሪክ ኪዩቢክ ውኃ አምርቶ ማሠራጨቱን የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ከገፀ-ምድር የውኃ መገኛዎች 56 ነጥብ 38 ሚሊየን ኪዩቢክ እንዲሁም ከከርሰ-ምድር ውኃ መገኛዎች 87 ነጥብ 43 ሚሊየን ሜትር ኪዩቢክ ውኃ አምርቶ በማሰራጨት ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡

በ2016 የበጀት ዓመት ከገፀ-ምድርና ከርሰ-ምድር ውኃ መገኛዎች 210 ነጥብ 94 ሚሊየን ሜትር ኪዩቢክ ውኃ በማምረት የከተማዋን ነዋሪ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ እየሠራ መሆኑንም አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.