Fana: At a Speed of Life!

በዱባይ የተከሰተው ጎርፍ በከተማዋ እንቅስቃሴ ላይ ከባድ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች በዱባይ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በከተማዋ እንቅስቃሴ ላይ ከባድ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተገለጸ።

በከተማዋ ወደ ዱባይ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ የሚወስደውን መንገድ ጨምሮ አውራ ጎዳናዎችና መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል።

የሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ በዘገባው እንደጠቀሰው ማክሰኞ ምሽት ላይ የጣለው ከባድ ዝናብ የአየር ሁኔታ ምዝገባ ከተጀመረበት ከፈረንጆቹ 1949 ጀምሮ ከፍተኛው ነው።

በከተማዋ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጥለው ዝናብ በ24 ሰዓት ውስጥ በመጣሉ ጉዳት ያስከተለ ጎርፍ መከሰቱን ሮይተርስ እና ስካይ ኒውስ በዘገባቸው ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.