Fana: At a Speed of Life!

ቤተልሔም ወልዴ በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ሻምፒዮና ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ከደቡብ አፍሪካ አቻዋ ጋር የተጋጠመችው ቤተልሄም ወልዴ በበቃኝ አሸንፋለች፡፡

የመላው አፍሪካ ሻምፒዮኗ ቤተልሄም ወልዴ በሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ሀይለኛ ቡጢ በማሳረፍ ነው በዳኛ ውሳኔ ያሸነፈችው፡፡

በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያን የወከሉት አቡዱሰላም አቡበከር፣ አቡበከር ሰፋን እና ኤርሚያስ መስፍን በተጋጣሚዎቻቸው መሸነፋቸውን ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.