Fana: At a Speed of Life!

ኤሌክትሪክ የማከፋፈል ስራ ዐቢይ አካል እንደመሆኑ ዘርፉ ሙሉ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል -ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤሌክትሪክ የማከፋፈል ስራ ዐቢይ አካል እንደመሆኑ ዘርፉ ሙሉ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥራ እና ክህሎት፣ መከላከያ፣ ማዕድን፣ ኢንዱስትሪ እና ኢኖቬሽን ሚኒስትሮች ጋር በመሆን በኢንዱስትሪዎች ጉብኝት አካሂደዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ ሀገር በቀል ኩባንያዎች ከፍተኛ ኃይል አስተላላፊ እና የኤሌትሪክ ገመዶችን በማምረት በሀይል አቅርቦት እና ቴሌኮም ኢንደስትሪ መሳተፋቸው እጅግ አበረታች ነው ብለዋል።

ኤሌክትሪክ የማከፋፈል ስራ ዐቢይ አካል እንደመሆኑ ዘርፉ ሙሉ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባልም ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ታምርት ሀሳብ ብቻ አይደለም፤ በማደግ ላይ ያለ ተግባራዊ እውነት፤ ኢንዱስትሪዎቹ በሀገር በቀል የተሽከርካሪዎች ምርት፣ በኃይል እና ቴሌኮም መለዋወጫ ምርት ዘርፍ እንደ ከፍ ያለ ኃይል ተሸካሚ የኤሌትሪክ ገመዶችን በማምረት ብሎም በጨርቃጨርቅ ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው ተብሏል።

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የኢኮኖሚያችን የማዕዘን ድንጋይ እንደመሆኑ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምርታማ በሆኑት የሀገር በቀል አምራቾች ስራ ላይ የትኩረት ብርሃን ፈንጥቆባቸዋል ሲል ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.