Fana: At a Speed of Life!

በማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ም/ሳጅን ሮማን አሰፋ ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ምክትል ሳጅን ሮማን አሰፋ ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች፡፡
ትናንት ምሽት ሀገሯን የወከለችው የአዲስ አበባ ፖሊሷ ምክትል ሳጅን ሮማን አሰፋ በ54 ኪሎ ግራም የናሚቢያ ተጋጣሚዋን በመጀመሪያው ዙር በበቃኝ አሸንፋለች፡፡
ውድድሩ እስከ ሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቀጥል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.