Fana: At a Speed of Life!

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላን ህልፈተ-ሕይወት በማስመልከት የኃዘን መግለጫ አስተላልፈዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በሃዘን መግለጫቸው፤ ጀኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ ለሀገራቸውና ለቀጣናው ሠላምና ደህንነት መረጋገጥ የነበራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር አስታውቀዋል።

እሳቸውና ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖችን ባጋጠመቸው የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ ህይወታቸው በማለፉ በራሳቸውና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ስም የተሰማቸውን ሃዘንመግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጀኔራል ፍራነኪስ ኦሞንዲ ኦጎላ ለኬኒያና ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላበረከቱት አስተዋጽኦና በጎ ሥራ ሁልጊዜ ሲታወሱ ይኖራሉ ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፤ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከኬኒያ ወንድም ህዝቦች ጋር መሆኑን አስረድተዋል።

በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መኮንኖች ቤተሰቦችና ወዳጆች በራሳቸውና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ስም መጽናናትን ተመኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.