Fana: At a Speed of Life!

አስተዳደራዊ ፍትሕ የማኅበራዊ ፍትሕ የማዕዘን ድንጋይ ነው – አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አስተዳደራዊ ፍትሕ የማኅበራዊ ፍትሕ የማዕዘን ድንጋይ ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ ገለጹ።

አፈ ጉባዔው ይህንን የገለጹት፤ በፍትሕ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በፌዴራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅና በሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዙሪያ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

የዜጎችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በተሟላ መንገድ ለመተግበር የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ የማይተካ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ባማከለ መንገድ የተዘጋጀ እና በመላ ሀገሪቱ ግብዓት ተሰብስቦበት የተዘጋጀ ፖሊሲ መሆኑን አፈ ጉባዔ ታገሠ መጥቀሳቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) የምክክር መድረኩን በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን የመድረኩን ዓላማም አስተዋውቀዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ በርካታ ባለድርሻ አካላት ታድመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.