Fana: At a Speed of Life!

ቢያንስ አንድ ቢሊየን መራጮች የሚሳተፉበት የህንድ ምርጫ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አንድ ቢሊየን ያህል ህንዳውያን ድምፅ ይሰጡበታል ተብሎ የሚጠበቀው የህንድ ጠቅላላ ምርጫ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በቢሊየን የሚቆጠሩ ድምፅ ሰጭዎችን በማስተናገድ በዓለም ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው የህንድ ምርጫ በፈረንጆቹ ሰኔ 1 ቀን 2024 ፍፃሜውን እንደሚያገኝ ተገልጿል፡፡

በምርጫው ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለሶስተኛ ጊዜ ለማሸነፍ እየተወዳደሩ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የህንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲን ለማሸነፍ ውህደት ፈጥረው እየተፎካከሩ ነው ተብሏል፡፡

በምርጫው ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የሚያሸነፉ ከሆነ ከቀድሞው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃዋህራል ኔይሩ በመቀጠል ለሶስት ዙር በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተመረጡ ሰው ይሆናሉ፡፡

በህንድ ጠቅላላ ምርጫ የስራ እድል ፈጠራ፣ የዋጋ ንረት፣ የሀይማኖት ፖለቲካ እና የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ ቁልፍ ጉዳዮች ሆነው መነሳታቸው ተመላክቷል፡፡

የምርጫው ውጤት በፈረንጆቹ ሰኔ 4 ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.