Fana: At a Speed of Life!

የውሃ አቅርቦትን በማሻሻል ኮሮናን ለመከላከል የሚያግዙ በ13 ሚሊየን ብር የተገዙ የውሃ ፓምፖች ለክልሎች ተከፋፈሉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ልማት ኮሚሽንና የልማት አጋሮች ኮሮናን ለመከላከል እና የውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል የሚረዱ በ13 ሚሊየን ብር የተገዙ 34 ፓምፖችን ለክልሎች ተከፋፈሉ።

በውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ነጋሽ ዋጌሾ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፥ የውሃ ልማት ኮሚሽንና የልማት አጋሮች የኮሮና ስርጭትን ለመግታት የውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል በጥምረት እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በማገገሚያና በማቆያ ማዕከላት የውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን የጠቆሙት ሚኒስትር ዲኤታው፥ ለክልሎች የተከፋፈሉት ፓምፖች ኮሮናን ለመዋጋት የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑን ገልጸዋል።

የውሃ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተርር በሻህ ሞገሴ በበኩላቸው፥ የኮቪድ19 ስርጭትን ለመከላከል በዓለም ባንክ ብድር ከሚሠራው የ23 ከተሞች ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ላይ ለ12 ከፍተኛ የውሃ ችግር ላለባቸው ከተሞችና የድምበር መውጫና መግቢያ ከተሞች 150 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ፓምፖች፣ ጄኔሬተሮች፣ ቧንቧዎችና የቧንቧ መገጣጠሚያዎች ለመግዛት ሂደት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የየክልሎቹ የስራ ሃላፊዎችም ፓምፖቹ የውሃ አቅርቦቱን ለማሻሻል ይረዳሉ ማለታቸውን ከውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.