Fana: At a Speed of Life!

በማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ ሚሊዮን ጨፎ የደቡብ አፍሪካ አቻዋን በበቃኝ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ እየተካሄደ ባለው የማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ሚሊዮን ጨፎ የደቡብ አፍሪካ አቻዋን በበቃኝ አሸንፋለች፡፡

በ60 ኪሎግራም የደቡብ አፍሪካ አቻዋን የገጠመችው ቦክሰኛዋ በውድድሩ ሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ባሰረፈችው ቡጢ በዳኛ ውሳኔ አማካኝነት በበቃኝ ማሸነፍ ችላለች።

ማሸነፏን ተከትሎም ቦከሰኛዋ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፏን ከኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ ሲሆን፤ የመላው አፍሪካ ሻምፒዮኗ ቤተልሄም ወልዴ እና ም/ሳጅን ሮማን አሰፋ ተጋጣሚዎቻቸውን በተመሳሳይ በበቃኝ ማሸነፋቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.