Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሜካናይዜሽን የልህቀት ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሜካናይዜሽን የልህቀት ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት ተቀመጠ።
 
በደቡብ ኮሪያ መንግስት ድጋፍ የሚገነባው ማዕከሉ የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂ ጥራት ለመፈተሽ፣ የአቅም ግንባታ ስራ እና ተያያዥ ተግባራትን ለማከናወን አገልግሎት እንደሚውል ተገልጿል።
 
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን በሚደረገው ጥረት የደቡብ ኮሪያ መንግስት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀው፤ የግብርና ሜካናይዜሽን የልህቀት ማዕከልን መገንባቱ የኢትዮጵያ መንግስትን የ10 ዓመቱን የግብርና መሪ ዕቅድ ለማሳካት አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
 
የዕቅዱ አንዱ ትኩረት የግብርና ሜካናይዜሽን በትኩረት መስራት እንደሆነም አመልክተዋል።
 
የደቡብ ኮሪያ የኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ሳንግ ዱዋ ኪም በበኩላቸው፤ መንግስታቸው የግብርና ሜካናይዜሽን የልዕቀት ማዕከልን በመገንባት ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያለውን ፍላጎት ገልፀዋል፡፡
 
የሕንፃ ዲዛይንና ቁጥጥርን በሃላፊነት እየመራ ያለው የዶሪ አርክቴክተስ ስራ አስፈፃሚ ጄኦንግ ሱኪም በበኩላቸው ማዕከሉ የግብርና ማሽነሪ ኢንዱስትሪን በማሳደግ ለአርሶ አደሩ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ጠቁመዋል።
 
ማዕከሉ የሚገነባው በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ሲሆን የግንባታው አጠቃላይ ወጪ 800 ሚሊዮን ብር መሆኑ በመርሐ ግብሩ ላይ መገለጹን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.