Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016/17 ምርት ዘመን 1 ሚሊየን 78 ሺህ 257 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፡፡

እስከ አሁን ባለው መረጃም በ20 መርከቦች 1 ሚሊዮን 116 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ መድረሱ ተመላክቷል፡፡

ጂቡቲ ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ውስጥ 96 ነጥብ 61 በመቶ የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ሲሆን፤ 37 ሺህ 792 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ በጅቡቲ ወደብ ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

በ62 የባቡር ምልልስ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው 1 ሚሊየን 78 ሺህ 257 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ከ120 በላይ ወደሆኑ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች በከባድ ተሽከርካሪዎች መጓጓዙም ተጠቁሟል፡፡

ዘንድሮ ከ60 ሺህ እስከ 96 ሺህ ሜትሪክ ቶን የመጫን አቅም ያላቸው በርካታ ግዙፍ መርከቦች ማዳበሪያውን ማጓጓዛቸውም ነው የተገለጸው፡፡

በቀጣዩ ሳምንትም 63 ሺህ 660 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ወደብ ትደርሳለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡21:30

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.