Fana: At a Speed of Life!

የጉራጌ ህዝብ ስለ አንድነት ያስተማረ፣ አንድነት ሃይል ነው ብሎ የሚያምን ህዝብ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉራጌ ህዝብ ስለ አንድነት ያስተማረ ፣ አንድነት ሃይል ነው ብሎ የሚያምን ፣በአንድት የሚገኘውን ፀጋ በልምድ ፣በሕይወቱ የተገነዘበ ነው ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

በርካታ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ የተገኙት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ÷ጉራጌ “ጎጎት”በተባለ ቃልኪዳኑ ስለ አንድነት ያስተማረ ፤ አንድነት ሃይል ነው ብሎ የሚያምን፤ በአንድት የሚገኘውን ፀጋ በልምድና በሕይወቱ የተገነዘበ ነው ብለዋል፡፡

እርስ በእርስ በማጋጨት እና በመከፋፈል አንድነታችን ለማጥፋት የሚሰሩ አካላት የህዝብ አንድነትን አንድነት ሀይል መሆኑን ከሚያምነው ጉራጌ ሊማሩ ይገባልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ጉራጌ ስለ ሰላም ያስተምራል ፤በሰላም ይኖራል ፤ሰላምን ያስተጋባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ሰላም ሳናስብ ሳንናገር ሰላምን ልንጎናፀፋት አንችልም ነው ያሉት፡፡

መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጉራጌ ህዝብ ተምሮ ሰላም የሰፈነባት አንድነቷ የተጠበቀ እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት በጋራ መቆም አለብት ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የእኛ የቋንቋ፣ የባህል፣የአቀማመጥ ልዩነት ኢትዮጵያን የሚበትን መሆን የለበትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ አንድነት እና አብሮነት ለመማር የጉራጌን ባህል መገንዘብ ጠቃሚ ነው ብለዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.