Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ወደ ፖላንድ ዋርሶው በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው 4 ሳምንታዊ በረራዎችን ማድረግ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

ዋርሶው በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) የተመዘገቡ ቅርሶች መገኛ፣ የድንቅ ኪነ ሕንፃዎች ማዕከል እና ታሪክንና ዘመናዊነትን አጣምራ የያዘች በዓለም በቱሪስት መዳረሻነታቸው ከሚጠቀሱ ቀዳሚ ከተሞች አንዷ ነች።

አየር መንገዱ ወደ እዚህች ከተማ ከሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ 4 ሳምንታዊ በረራዎችን ማድረግ ሊጀምር መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

አየር መንገዱ የበረራ ትኬት ለማግኘት ለሚፈልጉ ደንበኞቹ በአየር መንገዱ ተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ፣ ድረ ገጽ ወይም በትኬት ሽያጭ ቢሮዎች በመቁረጥ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.