Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ሐዋሳ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር የመስክ ምልከታና የስራ ግምገማ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ሐዋሳ ገብተዋል፡፡

ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች÷ ሐዋሳ ሲገቡ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞና የክልሉ የሥራ ሀላፊዎች በሐዋሳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የሥራ ሀላፊዎቹ በቆይታቸው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ስራዎችን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.