Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የኅብረት ሥራ ባዛርና ኤግዚቢሽን በመቀሌ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘የኅብረት ሥራ ማህበራት መጠናከር ለሰላምና እድገት’ በሚል መሪ ሀሳብ ሀገር አቀፍ የኅብረት ሥራ ባዛርና ኤግዚቢሽን በመቀሌ ተከፍቷል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ማህበራት ከአቻ ማህበራት ጋር መልካም ግንኙነትና የግብይት ትስስር እንዲፈጥሩ መድረኩ ሚና እንዳለው ተገልጿል፡፡

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የማህበራዊ ልማት ሴክሬታሪያት ካቢኔ ሀላፊ ክንደያ ገ/ህይወት (ፕ/ር)÷ መርሐ ግብሩ ለግብርና ቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያግዝ ልምድ ለመለዋወጥ ያስችላል ብለዋል።

የክልሉ የኅብረት ሥራና የገበያ ልማት ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ነጋ አሠፋ በበኩላቸው÷ማህበራቱን ወደ ስራ የመመለስ ስራ እየተሠራ መሆኑን በመግለጽ በቀጣይም ወደ ሪፎርም ስራ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በመክፈቻ መርሐ ግብሩ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ተሞክሮ፣ የክልሉ ኅብረት ስራ ዘርፍና የፋና ወጣቶች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ተሞክሮ እንዲሁም የድሬዳዋ ገበሬዎች ዩኒየን ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ተብሏል፡፡

በውይይቱ የሜካናይዜሽን አቅም ማጠናከር እና የብድር አቅርቦትን ማሳደግ አስፈላጊ ነው መባሉን ከኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የግል ዘርፉ፣ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ተመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.