Fana: At a Speed of Life!

በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ አዲስ አምራች ኩባንያ ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ባቲ ትሬዲንግ ኩባንያ የማምረቻ ሼድ ውስጥ ማምረቻ ማሽነሪዎችን በመትከልና በመገጣጠም ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ኩባንያውን በይፋ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

በዚሁ ወቅት አቶ አክሊሉ ታደሰ÷ ባቲ ትሬዲንግ ኩባንያ ኮርፖሬሽኑ አቅም ላላቸው ሀገር በቀል ኩባንያዎች የሰጠው ትኩረት ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

አቅም ያላቸው ሀገር በቀል ኩባንያዎችና ባለሀብቶች ኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ ያደረገውን ቀልጣፋ አሰራርና ማበረታቻዎችን በመጠቀም ወደ ኢንቨስትመንት እንዲመጡ ጋብዘዋል።

በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዛሬ ተመርቆ ስራ የጀመረው ባቲ ትሬዲንግ ከ350 ሚሊየን ብር በላይ ኢንቨስት በማድረግ ጥጥን እንደ ግብዓት በመጠቀም ክር የሚያመርት ነው ተብሏል፡፡

ለምርት ሂደቱ የሚረዳ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጣ የግብዓት ግዢ መፈጸሙንም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኩባንያው 300 ለሚደርሱ ዜጎች የስራ እድል እንደፈጠረ እና ምርቶችንም ሙሉ ለሙሉ ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የውጪ ምንዛሪን በማዳን በኩል ከፍተኛ ሚናን ይወጣል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.