Fana: At a Speed of Life!

በም/ጠ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ በሲዳማ ክልል የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ስራዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ በሲዳማ ክልል የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ስራዎችን ጎበኘ።

በጉብኝቱ ላይ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና የከተማ አስተዳደሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ ካስጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በተከናወኑ የንብ ማነብ፣ የወተትና የዶሮ መንደር ምስረታ ክልሎች ተጨባጭ ለውጥ አምጥተዋል።

የሲዳማ ክልልም በመርሐ ግብሩ እንደ ክልል የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ስምንት ኢኒሼቲቮችና 68 ፓኬጆች አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ገብቶ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.