Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ብሪታኒያ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ብሪታኒያ ስትራተጂካዊና ቅድሚያ በሚሰጣቸውን ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ።

በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የተመራው ልዑክ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ ስብሰባ ጎን ለጎን ከብሪታኒያ የአፍሪካ ልማት ምክትል ሚኒስትር አንድሪው ሚሼል ጋር ተወያይቷል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፤ ኢኮኖሚው የሀገር ውስጥና የውጭ ጫናን ተቋቁሞ ስለሚቀጥልበት፣ ብሪታኒያ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ስላላት ፍላጎት እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋትና ትብብር ስለምታደርገው ድጋፍ መክረዋል።

አንድሪው ሚሼል ሀገራቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ በበኩላቸው፤ ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ እያደረገች ላለው ያልተቋረጠ ድጋፍ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ብሪታኒያ በሰብዓዊ ድጋፍና በልማት አጀንዳ በተለይም በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ በመሰረተ ልማት፣ በሰብዓዊ ልማት እንዲሁም በግል ዘርፍ ኢንቨስትመንት ተሳትፎ እያደረገች እንደሆነ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ስትራተጂካዊና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ዘርፎች ላይ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር መስማማታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.