Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 190 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 190 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 190 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ÷ሰባቱ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ6 ሺህ 600 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.